❝ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው ❞ የዮሐንስ ራእይ 1:3
❝ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው❞ የዮሐንስ ራእይ 1:3

❝… ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ…❞ 2 ጴጥሮስ 1:19

የጽሁፍ አገልግሎት

ከትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት ዘርፎች መካከል አንደኛው:- መጽሐፍት፣ መጽሔቶችና በራሪ ጽሑፎችን ማዘጋጀት ነው። በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ የተጻፉ ጽሑፎችን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ።

ትራክት እና ብሮሸሮች

የድምጽና የተንቀሳቃሽ ምስል አገልግሎት

የድምጽና የተንቀሳቃሽ ምስል አገልግሎት ዘርፍ፣ በድምጽ እንዲሁም በፊልም የተደገፈ አገልግሎት ሲሆን፣ ዕለታዊ የቃለ-እግዚአብሔር ስብከት፣ ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ዘጋቢ ፊልሞች፣ የኢንተርኔት ሬዲዮ አገልግሎት እና የመሳሰሉት ይቀርቡበታል።

ዕለታዊ የጥሞና መልዕክቶች

ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት

ስብከቶች

ፊልሞች እና ዘጋቢ ቪዲዮዎች

የትንቢት ቃል Internet ሬዲዮ

የቤትና ቤተሰብ-ተኮር አገልግሎት

ቤተሰብ የማህበረሰብ ግንባታ መሰረት እንደሆነ እውቅና በመስጠት፣ የትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት ሶስት የቤትና ቤተስብ-ተኮር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

(1) ሐና 4 እስከ 14 አገልግሎት:- ስለ ክርስቲያናዊ የልጆች አስተዳደግ ጠቃሚ ትምህርቶች የሚቀርብበት ነው።

(2) የጽዮን እናት አገልግሎት:- ወላጆች ለልጆቻቸው ዘወትር የተለየ ጸሎት የሚያደርጉበትና አጫጭር መንፈሳዊ መልእክቶች የሚደመጥበት አገልግሎት ነው።

(3) የልጆች አገልግሎት:- ልጆች በመንፈሳዊ ሕይወት ለማደግ የሚጠቅሟቸው የተለያዩ መርሐ-ግብሮች የሚቀርብበት አገልግሎት ነው።

የጽዮን እናት አገልግሎት

ሐና 4-14 የቤተሰብ አገልግሎት

የልጆች አገልግሎት

ዕዝራ ሴሚናሪ

የ”ዕዝራ ሴሚናሪ” አገልግሎት ዘርፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሶች (ትምህርቶች) የሚሰጡበት የበይነ-ሙረብ ትምህርት ቤት ሲሆን፤ ሰልጣኞች እንደ ዕዝራ ቃሉን ለመመርመር፣ በቃሉ ለመኖርና፣ ቃሉን ለማካፈል የሚሰለጥኑበትና የሚተጉበት ዘርፍ ነው።

ዕዝራ ሴሚናሪ

የመዝሙር አገልግሎት

ከትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት ዘርፎች መካከል ሌላው፤ የዝማሬ አገልግሎት ሲሆን፣ በተለያዩ ዘማሪዎች የተዘመሩ መዝሙሮችን በዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ማግኘት ይችላሉ።

የህይወት ቃል

ይህ የቴሌግራም ቻናል በየእለቱ ህይወት ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል አጠር ያለ መልእክት የሚቀርብበት ነው። ይህንን ቻናል በመቀላቀልና አብረን ይህንን የህይወት ቃል እንድንመረምር እናድማችኋለን።

የህይወት ቃል / Word of life

ልዩ ፕሮግራሞችና ዝግጅቶች

ልዩ ዝግጅት 1

ልዩ ዝግጅት 2

ልዩ ዝግጅት 3